ዜናዎች።
በዓለ ጥምቀት።
ጥር ፲ ቀን ፳፻፫ ዓ. ም.
የተወደዳችሁ ምእመናን! እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።
ጾመ ገሃድ (ጋድ)፦ የቃሉ ትርጕም «ገሃድ» ሲል መገለጥ፥ «ጋድ» ሲል ለውጥ ማለት ነው። ቅዱሳን ሐዋርያት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱና የጥምቀቱ በዓል በሳምንት ሁለት ቀን በምንጾምባቸው ጾም በተሠራባቸው በረቡዕና በዓርብ የዋለ እንደ ሆነ የጾሙ ሥርዓት ሳይጠበቅ፤ . . .ተጨማሪ።
በዓለ ልደት።
ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻፫ ዓ. ም.
የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን! እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለ፳፻፫ ዓመተ ምሕረት በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!
ክቡር አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ስለ ጋድ (ገሃድ) እና ስለ በዓለ ልደት ያስተላለፉትን ትምህርት ...ተጨማሪ።
በዓለ ደመራና በዓለ መስቀል፡፡
መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፫ ዓ. ም.
የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን! እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለ፳፻፫ ዓመተ ምሕረት በዓለ ደመራና በዓለ መስቀል በሰላም አደረሳችሁ!
እነዚህን በዓላት በተመለከተ ክቡር አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ መስከረም ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ. ም. ያስተላለፉትን ትምህርት ከድምፅ ማኅደር አውርዳችሁ እንድታዳምጡ እንጋብዛለን። አምላካችን በዓሉን የተባረከ ያድርግልን፤ በረከተ መስቀሉን ይክፈለን፤ አሜን።
የዘመን መለወጫ በዓል፤ ዕንቍጣጣሽ።
መስከረም ፩ ቀን ፳፻፫ ዓ. ም.
የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን! እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለ፳፻፫ ዓመተ ምሕረት የዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ። እንደሚታወቀው አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ በሕይወት በነበሩ ጊዜ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ለምእመናን ይጠቅማል ያሏቸውን መልእክቶች ያስተላልፉ ነበር። እኛም ይህንን በማስታወስ እንዲሁም ለዕረፍታቸው ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ይህን በተለያዩ ጊዜአት ካስተማሯቸው ትምህርቶች የተጠናከረ ጽሑፍ አቅርበናል። ተጨማሪ።
ቤተ ክርስቲያናችንን ከውድቀት ለማንሣት እንጣር።
ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን።
ውጉዙና ዐመፀኛው ፓትርያርክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ቀን ከሌት ለሚያደርጉት ጥረት ማስታወሻ ወይም ማኅተም ይሆን ዘንድ፤ ወይንም ይህችን ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለማፍረሳቸው የእንኳን ደስ አለዎ ገጸ በረከት ይሆን ዘንድ በግብር አበሮቻቸው የተሠራላቸው ሐውልት ወይም ጣዖት በአካል በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ከቆመ እነሆ ቀናት ተቆጠሩ። እሳቸው ግን ቤተ ክርስቲያን የምትመራባቸውን ሕጎች ሁሉ ሽረው ቤተ ክርስቲያንን በሚመራው መንፈስ ቅዱስ ፈንታ ገብተው በጣዖትነት ከተሠየሙ ከ፲፬ ዓመት በላይ ሆኖአል። ተጨማሪ።
የክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ ዕረፍት ፫ኛ ዓመት መታሰቢያ።
ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን።
አባታችን አለቃ አያሌው ካረፉ እነሆ ሦስት ዓመታት ተቆጠሩ። በእነዚህ ሦስት ዓመታት በቤተ ክርስቲያናችን በኩል ያለው ችግር ከቀን ወደ ቀን እየባሰ ከመሄድ በስተቀር የተሻለ ነገር አልታየም። ይልቁንም በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ጣዖት እስከ መቆም ደርሷል። በክቡር አባታችን የቀረቡት ማስጠንቀቂያዎችም እየተፈጸሙ ይገኛሉ። የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖትና ሥርዓት ተበላሽቷል፤ ሲኖዶሱ ተጠሪነቱ ለመንፈስ ቅዱስ መሆኑ ቀርቶ ለፓትርያርኩ ሆኗል፤ በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያኒቱ የፓትርያርኩ የግል ርስት ሆናለች። ሊቃነ ጳጳሳት፥ ካህናትና ምእመናን ቤተ ክርስቲያንን ችላ ብለዋል። ተጨማሪ።
በዓለ ሐዋርያት።
ሐምሌ ፭ ቀን ፳፻፪ ዓ∙ ም∙
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን።
የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን! አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን ጾሙን በሰላም አስፈጽሞ የአባቶቻችንን የቅዱሳን ሐዋርያትን በዓል ለማክበር አበቃችሁ፡፡
ይህንን በዓልና ሌሎችም በሐምሌ ወር ውስጥ የሚታሰቡ በዓላትን በማስመልከት አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ሐምሌ ሐምሌ ፬ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ. ም. ያስተላለፉትን ትምህርት ከዚህ በማውረድ እንድታዳምጡት እንጋብዛለን፡፡
አምላካችን አገራችንን ይጠብቅልን፤ ከአባቶቻችን ከቅዱሳን ሐዋርያት በረከት ይክፈለን፤ አሜን!
ለፓትርያርክ አባ ጳውሎስ ሐውልት ሊቆም መታሰቡን በመቃወም የቀረበ መግለጫ።
ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
የተወደዳችሁ ምእመናን!
በቅርቡ በመገናኛ ብዙኃን (አዲስ አድማስ ጋዜጣ፥ ሰኔ ፳፮ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.) የቀረበውን ለፓትርያርክ አባ ጳውሎስ በአዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ሐውልት ሊቆም መታሰቡን በመግለጽ የቀረበውን ዜና በኀዘን አንብበናል። ይህ ሐሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፥ ሥርዓትና ባህል ውጪ በመሆኑ፤ በኢትዮጵያ አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የምንቃመው መሆኑን እየገለጽን ክቡር አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ የዛሬ ፲፬ ዓመት በገናናው ጋዜጣ አማካይነት ያስተላለፉትን ሁለተኛ ቃለ ግዝት እንድታነቡ እንጋብዛለን። ተጨማሪ።
በዓለ ጰራቅሊጦስ።
ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
የተወደዳችሁ ምእመናን! እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለ፳፻፪ ዓ. ም. በዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ።
አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ካስተላለፏቸው ስብከቶች መካከል ሰኔ ፭ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ. ም. በዓለ ጰራቅሊጦስን በማስመልከት ያስተላለፉትን ለዚህ በዓል መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ያቀረብን ስለ ሆነ ምእመናን ይህን ትምህርት ከዚህ አውርዳችሁ ወይም ከድምፅ ማኅደር እንድታዳምጡት እንጋብዛለን።
እግዚአብሔር አምላካችን በዓሉን የተባረከ ያድርግልን፤ አገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅልን፤ አሜን።
በዓለ ዕርገት።
ግንቦት ፭ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
የተወደዳችሁ ምእመናን! እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለ፳፻፪ ዓ. ም. በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ።
አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ካስተላለፏቸው ስብከቶች መካከል ግንቦት ፳፰ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ. ም. በዓለ ዕርገትን በማስመልከት ያስተላለፉትን ለዚህ በዓል መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ያቀረብን ስለ ሆነ ምእመናን ይህን ትምህርት ከዚህ አውርዳችሁ እንድታዳምጡት እንጋብዛለን።
እግዚአብሔር አምላካችን በዓሉን የተባረከ ያድርግልን፤ አገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅልን፤ አሜን።
በዓለ ልደታ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል ማርያም።
ግንቦት ፩ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
የተወደዳችሁ ምእመናን! እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለ፳፻፪ ዓ. ም. በዓለ ልደታ በሰላም አደረሳችሁ።
አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ በ፲፱፻፺፱ ዓ. ም. ካሳተሙት <<ዜና ሕይወት ዘቅድስተ ቅዱሳን እመ አምላክ>> ከተባለው መጽሐፍ ገጽ ፷፬ - ፹፪ የተገኘውን ጽሑፍ ለዚህ በዓል መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ያቀረብን ስለ ሆነ ምእመናን ይህን ጽሑፍ ከዚህ አውርዳችሁ እንድታነቡት እንጋብዛለን።
እግዚአብሔር አምላካችን በዓሉን የተባረከ ያድርግልን፤ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤትና በረከት ያድለን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን በአማላጅነቷ ታስብልን፤ አሜን።
በዓለ ትንሣኤ፤ ፋሲካ፤ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ።
መጋቢት ፳፮ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
«ተንሥአ በከመ ይቤ።» «እነሣለሁ እንዳለ ተነሣ።» (ማቴ፤ ም ፳፰፥ ቍ ፰።)
የተወደዳችሁ ምእመናን! እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለ፳፻፪ ዓ. ም. በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ። ይህንን በዓል በተመለከተ አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ሚያዝያ ፲፱ ቀን ፲፱፻፹፯ ዓ. ም. ያስተላለፉትን ትምህርት ከድምፅ ማኅደር ውሥጥ ማውረድ ይቻላል። በተጨማሪም ሚያዝያ ፲ ቀን ፲፱፻፺ ዓ∙ ም∙ ይህንን በዓል አስመልክተው ለኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ያስተላለፉትን መልእክት ከዚህ ማንበብ ይቻላል። አምላካችን በዓሉን የተባረከ ያድርግልን፤ በረከተ ትንሣኤውን ለመሳተፍ ያብቃን፤ አሜን።
ሰሙነ ሕማማት።
መጋቢት ፳ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
የተወደዳችሁ ምእመናን! እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለ፳፻፪ ዓ. ም. ሰሙነ ሕማማት በሰላም አደረሳችሁ። ይህንን ሳምንት በተመለከተ አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ሚያዝያ ፫ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓ. ም. ያስተላለፉትን እንዲሁም ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ. ም. ጸሎተ ኀሙስን በተመለከተ ያስተላለፉትን ትምህርት ከድምፅ ማኅደር ውሥጥ ማውረድ ይቻላል። አምላካችን ጾሙን በሰላም አስፈጽሞ ብርሃነ ትንሣኤውን ለማየት፥ በረከተ ትንሣኤውን ለመሳተፍ ያብቃን፤ አሜን።
የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለፓፓ ፒየስ ፲፪ኛ የቅድስና መዓርግ ለመስጠት ማሰቧን በመቃወም የቀረበ መግለጫ።
የካቲት ፱ ቀን ፳፻፪ ዓ∙ ም∙
የተወደዳችሁ ምእመናን! የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንዳስቀመጠው የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በሃይማኖት ከኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያን ከተለየችበት ጊዜ አንሥቶ የሮማን የቄሣር መንግሥት ጉልበት በማድረግ ካቶሊካውያን ያልሆኑ ክርስቲያኖችን በተለያዩ አሠቃቂ መንገዶች ከማጥቃት የቦዘነችበት ጊዜ የለም። ይልቁንም የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን። ይህም ግብሯ በዐፄ ሱስንዮስ ጊዜ በነበረው የሃይማኖት ጦርነት፥ ኋላም በዐድዋ ጦርነትና በ፭ቱ ዓመት የፋሺስት ጦርነት ጊዜ የታየና በታሪክ የተመዘገበ ነው። ተጨማሪ።
ዐቢይ ጾም።
የካቲት ፩ ቀን ፳፻፪ ዓ∙ ም∙
እንኳን ለ፳፻፪ ዓመተ ምሕረት ዐቢይ ጾም በሰላም አደረሰዎ። ክቡር አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ጾምን፥ በተለይም ዐቢይ ጾምን በተመለከተ «የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕግጋት» በተባለው መጽሐፋቸው ካሰፈሩት የተገኘውን ትምህርት ይህንን ታላቅ ጾም ምክንያት በማድረግ አቅርበናል። ተጨማሪ።
በዓለ አስተርእዮ።
ጥር ፳፩ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
መሠረተ ቃል፤ ‹‹ኵለንታኪ ሠናይት አንተ ኀቤየ፤ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ ላዕሌኪ። ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ አምሊባኖስ።» «የእኔ ሆይ ሁለንተናሽ ያማረ ነው፤ በአንቺ ላይም ምንም ምን ነውር የለብሽም። ከሊባኖስ ነዪ፤ እቴ ሙሽራ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ።›› (መኃ. ፬፥ ፯።)
እስከ አሁን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ ሳለች የተፈጸሙትን ሁኔታዎች አሳይተናል። ከዚህ ጀምሮ ግን የምንመለከታቸው ከሞት በኋላ ያሉትን ነው፡፡ ተጨማሪ።
ጋድ (ገሃድ) እና በዓለ ጥምቀት።
ጥር ፱ ቀን ፳፻፪ ዓ∙ ም∙
«ጾመ ገሃድ (ጋድ)፦ የቃሉ ትርጕም «ገሃድ» ሲል መገለጥ፥ «ጋድ» ሲል ለውጥ ማለት ነው። ቅዱሳን ሐዋርያት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱና የጥምቀቱ በዓል በሳምንት ሁለት ቀን በምንጾምባቸው ጾም በተሠራባቸው በረቡዕና በዓርብ የዋለ እንደ ሆነ የጾሙ ሥርዓት ሳይጠበቅ፤ ፩ኛ፤ ታኅሣሥ ፳፰ ቀን ለ፳፱ አጥቢያ፤ ፪ኛ፤ ጥር ፲ ቀን ለ፲፩ አጥቢያ በመንፈቀ ሌሊት ቅዳሴ እንዲፈጸምና ምእመናን በትንሣኤው የአከባበር ሥርዐት ዐይነት በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩ አዝዘዋል። ስለዚህ ሁለቱም ማለት የልደት፥ የጥምቀት ዋዜማ በጾም እንዲታሰብ ሆኗል። ተጨማሪ።
ገና፥ ልደቱ ለእግዚእነ።
ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
የተወደዳችሁ ምእመናን! እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
ልደቱ ለእግዚእነ። ይህ በዓል ሰውን በመልካችን በምሳሌአችን እንፍጠር ብሎ በጥንተ ፍጥረት የተናገረ እግዚአብሔር ቃል የሰውን ልጆች ለማዳን፤ «አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ።» «የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ እመጣለሁ፤» ሲል በሰጠው ተስፋ፤ ሰው ሆኖ ሥጋ ለብሶ ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ያለ አባት የተወለደበት ነው። ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደው እግዚአብሔር ቃል ወልደ አብ ድኅረ ዓለም ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም መወለዱና ወልደ ማርያም መባሉ ለሰው ልጆች ክብርና ሕይወት ስለ ሆነ፤ ሥጋ ቃልን ተዋሕዶ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ከሰማያውያን መላእክት፥ ከምድራውያን ኖሎት (እረኞች) ምስጋናን በግልጥ የተቀበለበትን፥ ለሰው ልጆች ዕርቅ የተመሠረተበትን ይህንን ታላቅ በዓል ኢትዮጵያ ከዓለም ክርስቲያኖች ጋራ በመተባበር ታከብረዋለች። (ዘፍ፤ ፲፰፥ ፲። ሉቃ፤ ፪፥ ፲፫ - ፲፱።) ተጨማሪ።
በዓለ ቍስቋም።
ኅዳር ፮ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
«ቀላይ ለቀላይ ትጼውዖ በቃለ አስራቢከ።» «በፏፏቴ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራለች።» (መዝ፤ ፵፩ ፥ ፯።)
ታሪካዊ ንጽጽር ያላቸውን ጊዜዎች፥ ቦታዎች፥ ምክንያቶች በሚመለከት የተነገረ ቃል ነው። በተለይ መተርጕማን አበው፤ በሙሴና በኢያሱ ዘመን በኤርትራ፥ በዮርዳኖስ የተደረገውን ተአምር፥ ከዚያም ዐልፎ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ጊዜ የሆነውን ለመግለጽ ሰፊና ጥልቅ ትምህርት ሰጥተውበታል። የእኔ አስተሳሰብ ይህን አይመለከትም። እንደምታውቁት ዛሬ ኅዳር ፮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስንና የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ወደ ግብጽ መሰደድና በጊዜው ፍጻሜም ወደ ምድረ እስራኤል መመለሳቸውን መታሰቢያ በዓል የምታደርግበት ዕለት ነው። ይህ በዓል በቤተ ክርስቲያናችን ስያሜ ቍስቋም እየተባለ ይጠራል። ተጨማሪ።
ዘመነ መስቀል።
መስከረም ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.
የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን! እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለ፳፻፪ ዓመተ ምሕረት የመስቀል በዓል አደረሳችሁ። እንደሚታወቀው አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ በሕይወት በነበሩ ጊዜ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ለምእመናን ይጠቅማል ያሏቸውን መልእክቶች ያስተላልፉ ነበር። እኛም ይህንን በማስታወስ በዓለ መስቀልን ምክንያት በማድረግ በ፲፱፻፺ ዓመተ ምሕረት መስከረም ፳፩ ቀን በኢትኦጵ ጋዜጣ አማካይነት ለምእመናን ያስተላለፉትን መልእክት አቅርበናል።
እግዚአብሔር አምላካችን በዓሉን የተባረከ ያድርግልን። ዘመኑንም የሰላም፥ የጤና፥ የፍቅር፥ የሃይማኖት እንዲያደርግልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን፤ አሜን። ተጨማሪ።
ዕንቍጣጣሽ፥ ርእሰ ዐውደ ዓመት።
መስከረም ፩ ቀን ፳፻፪ ዓ∙ ም∙
የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን! እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለ፳፻፪ ዓመተ ምሕረት የዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ። እንደሚታወቀው አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ በሕይወት በነበሩ ጊዜ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ለምእመናን ይጠቅማል ያሏቸውን መልእክቶች ያስተላልፉ ነበር። እኛም ይህንን በማስታወስ እንዲሁም ለዕረፍታቸው ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ይህን በተለያዩ ጊዜአት ካስተማሯቸው ትምህርቶች የተጠናከረ ጽሑፍ አቅርበናል።
እግዚአብሔር አምላካችን በዓሉን የተባረከ ያድርግልን። መጪውንም ዘመነ ማርቆስ የሰላም፥ የጤና፥ የፍቅር፥ የሃይማኖት እንዲያደርግልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን፤ አሜን። ተጨማሪ።
የታላቁ መንፈሳዊ አባትና ሊቅ የአለቃ አያሌው ታምሩ ዕረፍት ፪ኛ ዓመት መታሰቢያ በደማቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዐት ተከበረ።
ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፩ ዓ∙ ም∙
የክቡር አባታችን የአለቃ አያሌው ታምሩ ዕረፍት ፪ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፩ ዓ ም በደማቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዐት ተከብሮ ዋለ።
በዕለቱ ከጠዋቱ ፬ ሰዓት ላይ በደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የክቡርነታቸው መቃብር በሚገኝበት ስፍራ ላይ ካህናተ እግዚአብሔር፥ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፥ ቤተሰብ፥ ወዳጅና ዘመድ እንዲሁም ተማሪዎቻቸው በተገኙበት የጸሎት ሥነ ሥርዐት ተካሂዷል።
በመቀጠልም ታላቁ አባት ለ፴፯ ዓመታት በኖሩበት፥ በጸለዩበት፥ በግዞት በኖሩበትና ጉባኤ ወንጌል ባካሄዱበት መኖሪያ ቤታቸው በመሄድ ጸሎተ ፍትሐት ተከናውኗል።በዚሁ ጊዜ የክቡር አባታችንን ሕይወት የሚያዘክሩ ቅኔዎችና ዝማሬዎች ቀርበዋል። የቅኔዎቹና የዝማሬዎቹ ምስጢርና ውበት የሥነ ሥርዐቱን ታዳሚዎች ልብ የነካ ነበር። ተጨማሪ።
ጾመ ፍልሰታ።
ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፩ ዓ∙ ም∙
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰዎ። ጾመ ፍልሰታ እንደሚታወቀው በአገራችን ዐዋቂዎች ብቻ ሳይሆኑ ሕፃናት ሳይቀሩ የሚጾሙት ጾም ነው። ጾሙም ብዙ ጸጋና በረከት የሚያሰጥ ነው። ተጨማሪ።
በዓለ ትንሣኤ።
ሚያዝያ ፲፩ ቀን ፪ሺ፩ ዓ∙ ም∙
«ተንሥአ በከመ ይቤ።» «እነሣለሁ እንዳለ ተነሣ።» (ማቴ፤ ም ፳፰፥ ቍ ፰።)
ሰው እግዚአብሔር የሰጠውን ትእዛዝ በመተላለፉ ምክንያት በሕይወቱ ሞት ተፈረደበት። «አንተ መሬት ነህ፤ ወደ መሬት ትመለሳለህ፤» ተባለ።
ማንኛውም ወንጀለኛ በሠራው ጥፋት ሲፈረድበት ሁለት ዐይነት መቀጫ አለ። ከእነዚህም አንዱ ሕግን በመተላለፉ የሚከፍለው መቀጫ ሲሆን፤ ሁለተኛው ለተበዳዩ የሚከፍለው ካሣ ነው። አዳም ሕግን በመተላለፉ በሥጋው ወደ መቃብር፥ በነፍሱ ወደ ሲኦል መውረድ ተፈርዶበት በሞተ ሥጋ፥ በሞተ ነፍስ ተቀጣ። ካሣ ግን የሚከፍለው አልነበረውምና እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ካሠለት። ስለዚህም ከሕይወት ወደ ሞት እንደ ሄደ ከሞት ወደ ሕይወት መመለስ ያስፈልገው ነበር። ስለዚህ ሰው የሆነው አምላክ በሞቱ ሞትን አጠፋለት። በመቃብሩም ሙስና መቃብርን አስቀረለት። በትንሣኤውም ትንሣኤን መሠረተለት። ይህን የቤዛነት ሥራ ለመፈጸም ክርስቶስ የሄደበትን የመስቀል ጉዞ ስንመረምር ከመሥዋዕትነቱ ማለት ከስቅለቱ፥ ከሞቱ ተነሥተን ትንሣኤውን ዕርገቱን እናያለን። ለሰውም የሰጠውን አዲስ ሕይወት እንመለከታለን። ተጨማሪ።
ሰሙነ ሕማማት።
ሚያዝያ ፭ ቀን ፪ሺ፩ ዓ∙ ም∙
ለ፪ ሺ ፩ ዓመተ ምሕረት ሰሙነ ሕማማት እንኳን አደረሰዎ። ሰሙነ ሕማማትን በተመለከተ አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ካስተላለፏቸው ስብከቶች መካከል አንዱን ከድምፅ ማኅደር ውስጥ ማግኘት ይችላሉ። አምላካችን ጾሙን በሰላም አስፈጽሞ ብርሃነ ትንሣኤውን ለማየት ያብቃን። አሜን።
ዐቢይ ጾም።
የካቲት ፲፫ ቀን ፪ሺ፩ ዓ∙ ም∙
እንኳን ለ፪ሺ፩ ዓመተ ምሕረት ዐቢይ ጾም በሰላም አደረሰዎ። ክቡር አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ጾምን፥ በተለይም ዐቢይ ጾምን በተመለከተ «የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕግጋት» በተባለው መጽሐፋቸው ካሰፈሩት የተገኘውን ትምህርት ይህንን ታላቅ ጾም ምክንያት በማድረግ አቅርበናል። ተጨማሪ።
እንዲሁም ክቡር አባታችን የ፲፱፻፺ ዓመተ ምሕረትን ዐቢይ ጾም ምክንያት በማድረግ ለኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፺ ዓመተ ምሕረት በወጣው ማዕበል ጋዜጣ አማካይነት ያስተላለፉትን መልእክት ከዚህ ማንበብ ይቻላል።
እግዚአብሔር አምላካችን ጾሙን በሰላም አስፈጽሞ ብርሃነ ትንሣኤውን ለማየት ያብቃን። አሜን።
በዓለ ጥምቀት።
ጥር ፲ ቀን ፪ሺ፩ ዓ∙ ም∙
ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለ፪ሺ፩ ዓመተ ምሕረት በዓለ ልደትና በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሰዎ። በዓለ ልደትን በተመለከተ ክቡር አባታችን ከሰጧቸው መግለጫዎች አንዱን በዚህ ድረ ገጽ ላይ ለማቅረብ ያቀድን የነበረ ቢሆንም በበዓሉ ሰሞን በነበረው የኢንተርኔት መሥመር መጣበብ ምክንያት ያቀድነውን ለማድረግ ባለ መቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለን። አሁን ግን በዓለ ጥምቀትን በማስመልከት ክቡር አባታችን ጥር ፲፪ ቀን ፲፱፻፺፮ ዓመተ ምሕረት በኢትዮጵ ጋዜጣ አማካይነት ለኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ያስተላለፉትን መልእክት ያቀረብን ስለ ሆነ በጥሞና እንዲያነቡት እንጋብዛለን። እግዚአብሔር አምላካችን በዓሉን የተባረከ ያድርግልን፤ ለአገራችንም ሰላምንና ብልጽግናን ያድልልን፤ አሜን። ተጨማሪ።
ዕንቍጣጣሽ፥ ርእሰ ዐውደ ዓመት።
መስከረም ፩ ቀን ፪ሺ፩ ዓ∙ ም∙
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገረዎ!
በአገራችን በኢትዮጵያ በደማቅ ሥነ ሥርዐት ስለሚከበረው ስለዚህ ታላቅ በዓል አባታችን ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ «የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕግጋት» በተባለው መጽሐፋቸው ከገጽ ፪፻፴፫ - ገጽ ፪፻፴፭ ያሰፈሩትን ከዚህ ማግኘት ይችላሉ።
«የዘመን መለወጫ በዓል የታወቀው ፫ ዐይነት ነው። አንደኛ እስራኤል በብሉይ ኪዳን ያከብሩት የነበረው ሚያዝያ ፩ ቀን፤ ሁለተኛ የዓለም ክርስቲያን የክርስቶስን ልደት ተቀዳሚ በማድረግ የሚያከብሩት ጥር ፩ ቀን፤ ሦስተኛ ኢትዮጵያ ጥንት መሠረቱን መሠረትነቱን ዐውቃ የምታከብረው መስከረም ፩ ቀን ነው። እስራኤል የዘመን መለወጫ በዓልን በሚያዝያ ማድረጋቸው፤ በዚሁ ወር ከግብጽ ባርነት ነጻ ስለ ወጡና እግዚአብሔር ይህንን የነጻነት በዓል በየዓመቱ እንዲያከብሩ ስላዘዛቸው መሆኑና የዓለም ክርስቲያን ጥር ፩ ቀን ማክበራቸው የክርስቶስን ልደት ምክንያት በማድረግ መሆኑ የታወቀና ብዙ ማተት የማያሻው ስለ ሆነ፤ ለወጣቶች አስቸጋሪ መስሎ ስለሚታያቸው ስለ ኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም ፩ ቀን ዐሳባችንን እንሰጣለን። ተጨማሪ።
የክቡር አባታችን የአለቃ አያሌው ታምሩ ዕረፍት ፩ኛ ዓመት መታሰቢያ በደማቅ ሥነ ሥርዐት ተከበረ።
ነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻ ዓ∙ ም∙
ነሐሴ ፲፬ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓመተ ምሕረት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የክቡር አባታችን የአለቃ አያሌው ታምሩ ዕረፍት ፩ኛ ዓመት መታሰቢያ ቅዳሜ ነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻ ዓመተ ምሕረት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሩሲያ የሳይንስና የባህል ማእከል ፑሽኪን አዳራሽ ከ፫፻፶ የማያንሱ ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዐት ተከበረ። ተጨማሪ።
ጾመ ፍልሰታ።
ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻ ዓ∙ ም∙
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰዎ። ጾመ ፍልሰታ እንደሚታወቀው በአገራችን ዐዋቂዎች ብቻ ሳይሆኑ ሕፃናት ሳይቀሩ የሚጾሙት ጾም ነው። ጾሙም ብዙ ጸጋና በረከት የሚያሰጥ ነው። ተጨማሪ።
|