መግቢያየሕይወት ታሪክመጻሕፍትየድምፅ ማኅደርቃለ ውግዘትግምጃ ቤት
 


ገና፥ ልደቱ ለእግዚእነ።
ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.

የተወደዳችሁ ምእመናን! እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።

ልደቱ ለእግዚእነ። ይህ በዓል ሰውን በመልካችን በምሳሌአችን እንፍጠር ብሎ በጥንተ ፍጥረት የተናገረ እግዚአብሔር ቃል የሰውን ልጆች ለማዳን፤ «አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ።» «የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ እመጣለሁ፤» ሲል በሰጠው ተስፋ፤ ሰው ሆኖ ሥጋ ለብሶ ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ያለ አባት የተወለደበት ነው። ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደው እግዚአብሔር ቃል ወልደ አብ ድኅረ ዓለም ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም መወለዱና ወልደ ማርያም መባሉ ለሰው ልጆች ክብርና ሕይወት ስለ ሆነ፤ ሥጋ ቃልን ተዋሕዶ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ከሰማያውያን መላእክት፥ ከምድራውያን ኖሎት (እረኞች) ምስጋናን በግልጥ የተቀበለበትን፥ ለሰው ልጆች ዕርቅ የተመሠረተበትን ይህንን ታላቅ በዓል ኢትዮጵያ ከዓለም ክርስቲያኖች ጋራ በመተባበር ታከብረዋለች። (ዘፍ፤ ፲፰፥ ፲። ሉቃ፤ ፪፥ ፲፫ - ፲፱።)

መሠረቱም፤ «እነሆ በኤፍራታ በጎል ተጥሎ፥ በጨርቅ ተጠቅልሎ አገኘነው፤ በግዕዘ ሕፃናት ሲያለቅስ ሰማነው፤ እንግዲህስ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብተን የጌታችን እግር ከቆመበት እንሰግዳለን፤» የሚለው ትንቢታዊ ቃል ነው። (መዝ፤ ፻፴፪፥ ቍ ፮ እና ፰።)

(የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕግጋት፤ ገጽ ፪፻፴፭)

በተጨማሪ ክቡር አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ በዓለ ልደትን በማስመልከት ታኅሣሥ ፳፯ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ. ም. ያስተላለፉትን ትምህርት ለማውረድ እዚህ ላይ ይጫኑ። ወይም የድምፅ ማኅደርን ይጎብኙ።

 

ተጨማሪ ገጾች።
 ዜናዎች
 አስተያየቶትን ይጻፉልን
 የ aleqayalewtamiru.org አባል ይሁኑ
ይህንን ገጽ ለወዳጆችዎ ያሳውቁ።
የኒውስሌተራችን ተጠቃሚ ይሁኑ
በየጊዜው የሚደረጉ ለውጦችን ለማወቅ ይመዝገቡ።
ሙሉ ሥም
የኢሜይል አድራሻ
መውረድ የሚችሉ ፋይሎች
የክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ የመንፈቅ መታሰቢያ። (.zip, 28.3 MB)
የክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ የመንፈቅ መታሰቢያ። (light weight) (.zip, 2.4 MB)
Unable to read the text?
Download Font (nyala.ttf, 427KB)
For PC users: download and save the font file in "C:\Windows\Fonts" folder and restart your browser
(Nyala.ttf, © 2006 Microsoft Corporation. All Rights Reserved. Nyala is either a registered trademark or a trademark of Microsoft Corporation in the United States and/or other countries.)
መግቢያየሕይወት ታሪክመጻሕፍትየድምፅ ማኅደርቃለ ውግዘትግምጃ ቤት
Copyright  , aleqayalewtamiru.org