"... አባ ጳውሎስ ድንገት ቢሞቱ፥ እኔም ድንገት ብሞት ያሉት ጳጳሳት፥ ያሉት ቀሳውስት ተተክተው የሚሠሩት ሥራ ምንም ዋጋ የለውም። ፍርድ ሳይፈረድ፥ አጥፊውና አልሚው ሳይለይ በምንም ዐይነት የሚደረገው ነገር ሁሉ ዋጋ የለውም። . . . አንድ ጳጳስ ለመሾም እነዚህ በዚያ ሕግ ላይ የፈረሙት ጳጳሳት ሁሉ የመሾም መብት ስለ ሌላቸው፤ በዚያ ሕግ ላይ ያልፈረሙ ሦስት ጳጳሳት ከሌሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንደገና ፓትርያርክ መሾም አትችልም።" . . .