ይህ በየዕለቱ ማታ ማታ በዜማ የሚደረስ ነው። በጾመ ፍልሰታ ብቻ ሳይሆን ዘወትርም ይጸለያል። ዕለቱም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ነው። በኢትዮጵያ አቆጣጠር አንድ ዕለት ሌሊቱ ይቀድማል ቀኑ ይከተላል። በአሁኑ ጊዜ ይህ የተዛባ ይመስላል። ስለዚህ ለምሳሌ የሰኞ ውዳሴ ማርያም የሚጸለየው እሑድ ማታ ነው። በተመሳሳይ የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም የሚጸለየው ሰኞ ማታ ይሆናል። የሌሎቹም ቀኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ይሄዳል።
ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ በ፲፱፻፺፬ ዓ፤ ም፤ ጾመ ፍልሰታ ውዳሴ ማርያምን በዜማ ሲያደርሱ ከተቀረፀው እነሆ።
ይህ በተለይ በጾመ ፍልሰታ የሚጸለይ ነው። የሚተረጐመውም ማለዳ በጧት ነው።
ነሐሴ አንድ ቀን መቅድሙ መጀመሪያ ተተርጕሞ የዕለቱ ውዳሴ ማርያም ትርጕም ይከተላል። መቅድሙ ከሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጕም ቀድሞ እንዲሁ ይተረጐማል። ነሐሴ ፲፭ ቀን ደግሞ ከዕለቱ ውዳሴ ማርያም ትርጕም ቀጥሎ ስለ እመቤታችን ዕረፍት፥ ትንሣኤና ስለ ጾመ ፍልሰታ አጀማመር የሚተርከው ታሪክ ይነገራል።
ከነሐሴ ፩ እስከ ነሐሴ ፲፬ ባሉት ቀናት ቅዳሴ ማርያም ለ፲፬ ክፍል ተከፋፍሎ ከየዕለቱ ውዳሴ ማርያም ትርጕም ቀጥሎ ይተረጐማል።
ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ በ፲፱፻፺፰ ዓ፤ ም፤ ጾመ ፍልሰታ ውዳሴ ማርያምን ሲተረጕሙ ከተቀረፀው እነሆ።