መግቢያየሕይወት ታሪክመጻሕፍትየድምፅ ማኅደርቃለ ውግዘትግምጃ ቤት
 


ወደ ግብጽ መሄድ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመራር ላይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተደጋጋሚ የተከሰቱትን የሃይማኖት ትምህርትና የሥርዓት መበላሸት በማስመልከት የቤተ ክርስቲያኒቱ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ የነበሩት አለቃ አያሌው ታምሩ ችግሩ ሥር ሳይሰድ ገና ከጅምሩ እንዲታረም ማሳሰቢያና ተማጽኖ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ ተማጽኖ አቅርበው ነበር። ነገር ግን ጥያቄአቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ዘንድ በቸልታ በመታየቱ ምክንያት፤ አለቃ አያሌው ታምሩ ባላቸው ከፍተኛ ሥልጣንና ኀላፊነት፤ በቤተ ክርስቲያን ላይ ዐመጽ የሚፈጽሙትን ፓትርያርኩንና ተከታዮቻቸውን ማውገዛቸው ይታወቃል። ቃለ ግዝታቸው በመጀመሪያ የወጣው ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት በ«መብሩክ» ጋዜጣ ላይ ነበር። ሙሉውን ቃለ ውግዘት ለማንበብ ከዚይ ይጫኑ።

አባታችን ይህን ቃለ ውግዘት ካስተላለፉበት ጊዜ ጀምሮ፤ ከምእመናንና ከተለያዩ ክፍሎች ውግዘቱን አስመልክቶ የተለያዩ ጥያቄዎች በቃልና በጽሑፍ፥ እንዲሁም በተለያዩ ጋዜጦች ላይ የቀረቡላቸው ሲሆን፤ ለቀረቡት ጥያቄዎችም ተገቢ የሆኑ ምላሾችን ሰጥተዋል ሰጥተዋል። በተለያዩ ጊዜዎች ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል በ፲፱፻፺ ዓ. ም. ብዙ ምእመናን በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝተው በጋራ ያቀረቡላቸው ሲሆን፤ ከእነዚህ ጥያቄዎች መካከል አንዱ፤ "በዚህ ውግዘት መካከል በስዎ ወይም በሳቸው መካከል የመለየት ባሕርይ ቢኖር ውግዘቱ እንደ ታሰረ ነው ወይስ እንደ ተፈታ ነው [የሚቆየው]? [ውግዘቱን] ማን ይፈታዋል? እስመ መቼ ድረስ ነው [ውግዘቱ የሚቆየው]?" የሚል ሲሆን፤ ክቡር አባታችን የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተው ነበር።

"[ውግዘቱ] እንደ ታሰረ ነው [የሚቆየው]፤ ማንም አይፈታውም። ቤተ ክርስቲያኒቱ እስከ ተመለሰች ድረስ [ውግዘቱ ይቆያል]። ቤተ ክርስቲያኒቱ ተመልሳ ሲኖዶሱ የቤተ ክርስቲያን፥ የክርስቶስ ተጠሪ ካልሆነ ምን ጊዜም አይፈታም። የክርስቶስ የሆኑ ጳጳሳት ከሌሉ፥ ካልተሾሙ፤ አሁን ያሉት [ጳጳሳት] አንዲያውም አይሆኑም፤ አሁን ያሉት አይሆኑም፤ ያሉት ካህናትም አይሆኑም፤ ይህን ዕወቁ። ለዚህ መድኃኒቱ ምእመናን ተሰብስበው ካህናቱንም አስገድደው፤ እሺ ያላቸውን በውድ፥ እምቢ ያላቸውን በግድ ለይተው አስወጥተው፤ አሁንም አባ ጳውሎስን አውግዘው፥ ራሳቸውን አስተካክለው ካልቆሙ በስተቀር ቤተ ክርስቲያን አሁንም የለችም፤ እንዲህ በመላም ደግሞ አትመለስም። ይህን ዕወቁ። በመላም አትመለስም። አባ ጳውሎስ ድንገት ቢሞቱ፥ እኔም ድንገት ብሞት ያሉት ጳጳሳት፥ ያሉት ቀሳውስት ተተክተው የሚሠሩት ሥራ ምንም ዋጋ የለውም። ፍርድ ሳይፈረድ፥ አጥፊውና አልሚው ሳይለይ በምንም ዐይነት የሚደረገው ነገር ሁሉ ዋጋ የለውም። ለዚህ ነው የጮኽኩት፤ ዓመት ሙሉ የሰው ያለህ የምል በዚህ ምክንያት ነው። ነገሩ ጥብቅ ስለ ሆነ፥ ከባድ ስለ ሆነ ነው። ሰውማ እኮ ቢኖረን ኖሮ፥ [ከአባ ጳውሎስና ከግብር አበሮቻቸው] የተለየ ሰው ሁለት ሦስት ሰው እንኳ ቢኖር ይሆን ነበር። ሌላ ቀርቶ አባ ጳውሎስ ቢሞቱ አንድ ጳጳስ ለመሾም እነዚህ በዚያ ሕግ ላይ የፈረሙት [ጳጳሳት] ሁሉ የመሾም መብት ስለ ሌላቸው፤ [በዚያ ሕግ ላይ] ያልፈረመ ጳጳስ ሦስት ከሌለ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንደገና ፓትርያርክ መሾም አትችልም። ይህን ዕወቁ። አትችልም። እንደገና ወደ ግብጽ መሄድ ነው።"

በወቅቱ የቀረቡት ጥያቄዎች በርካታ ሲሆኑ፤ እንደ አግባቡ መልስ ተሰጥቶባቸዋል። እኛም እነዚህ ጥየቄዎችና መልሶች አሁን ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለችበትን ሁኔታ የሚያመላክቱና መፍትሔ የሚጠቁሙ ሆነው ስላገኛናቸው ለእናንተ ለምእመናን ለማቅረብ ወደድን። ሙሉ ጥያቄዎቹንና የተሰጡትም መልሶች ለማዳመጥ ከዚህ ይጫኑ።

 

ተጨማሪ ገጾች
 ዜናዎች
 አስተያየቶትን ይጻፉልን
 የ aleqayalewtamiru.org አባል ይሁኑ
ይህንን ገጽ ለወዳጆችዎ ያሳውቁ።
የኒውስሌተራችን ተጠቃሚ ይሁኑ
በየጊዜው የሚደረጉ ለውጦችን ለማወቅ ይመዝገቡ።
ሙሉ ስም
የኢሜይል አድራሻ
መውረድ የሚችሉ ፋይሎች
የክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ የመንፈቅ መታሰቢያ። (.zip, 28.3 MB)
የክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ የመንፈቅ መታሰቢያ። (light weight) (.zip, 2.4 MB)
Unable to read the text?
Download Font (nyala.ttf, 427KB)
For PC users: download and save the font file in "C:\Windows\Fonts" folder and restart your browser
(Nyala.ttf, © 2006 Microsoft Corporation. All Rights Reserved. Nyala is either a registered trademark or a trademark of Microsoft Corporation in the United States and/or other countries.)
 
መግቢያየሕይወት ታሪክመጻሕፍትየድምፅ ማኅደርቃለ ውግዘትግምጃ ቤት
Copyright  , aleqayalewtamiru.org